የኒኦ ሶሳይቲ አባል መሆን ይቻላል። ነገር ግን መዘመን ያስፈልጋል። አዎንታዊነት ትልቅ ቦታ አለው። የኒኦ ሶሳይቲ መስፈርቶችን ማሟላትም ግድ ይላል። እንዲሁም የኒኦ ሶሳይቲ መተዳደርያ ደንቦችንና ስነ- ምግባር ሕግጋቶችን ማክበር አባልነት ያስገድዳል። በኒኦ ሶሳይቲ ውስጥ ደባል የሆኑ ማናቸውንም አፈንጋጭ ሃሳቦችን ማንጸባረቅ አይቻልም። ጽንፍ-ረጋጭነት ከመሀል ያወጣል።ፍትሓዊነትና ሰዋዊነት ማዕከልነት ነው። ለኒኦ ሶሳይቲ አባልነት በአእላፍ ደጀን ኔትዎርክ ውስጥ የሚደረጉ መልካም ንግግሮችና በጎ አመለካክቶች እንዲሁም ከሰብአዊነት የመነጩ በጎ ተግባሮችና ኢትዮጵያዊ አመለካከት: ለመለወጥ ደፋርነት መነሻ መስፈርቶች ይሆናሉ::
መልካም አባልነት!!
የኒኦ ሶሳይቲ አባልነት
1.በጸደቀው በኒኦ ሶሳይቲ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በሥራ አመራር ምክር ቤት እና በተዋረድ ባሉት የሥራ አስፈጻሚዎች አማካይነት አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታዎች ተሟልተው ሲቀርቡ እና በኒኦ ሶሳይቲ ጠቅላላ ጉባዔ ውሣኔ ተቀባይነት ያገኙ አባላት የሶሳይቲው አባላት ይሆናሉ ።
2. የኒኦ ሶሳይቲ አባል ለመሆን ፍላጎት ያደረበትና የኒኦ ሶሳይቲ የሥራ አስፈፃሚ የአባላት ቅበላ መመሪያን በተከተለ አግባብ በሙሉ ፍላጎቱ የኒኦ ሶሳይቲው አባል ለመሆን ስርዓቱን በተከተለ አግባብ ያመለከተ፣ ማናቸውንም መመዘኛዎችንና መስፈርቶችን የሚያሟላ መደበኛ አባል መሆን ይችላል፡፡
3. በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት እና በስራ አስፈፃሚው ተዘጋጅቶ በስራ አመራር ምክርቤቱ በሚፀድቀው የአባላት ምልመላ፤ ቅበላና አስተዳደር መመሪያ መሰረት በስራ አስፈፃሚው ተቀባይነት ያገኘ፤ በመመሪያው ድንጋጌ መሰረት በተጠቀሰ የምርመራና የቅበላ ጊዜ ውስጥ ከእጩ አባላት የሚጠበቁ ተግባሮችን አሟልቶ እንደተገኘ ፤ ጉዳዩ በሚመለከተው የሥራ አስፈፃሚው አካል ሲታመንበት እና በሥራ አስፈፃሚው ለመደበኛ አባልነት ታጭቶ ስሙ ለኒኦ ሶሳይቲው የሥራ አመራር ምክርቤት ቀርቦ ሲፀድቅ ፤ በመጨረሻም በአባላት ቅበላ እና አስተዳደር መመሪያዎች መሠረት ሊፈፅም የሚገባውን ከፍያ የፈፀመ አባል ሆኖ ይመዘገባል። ወይም እራሱን በድረ- ገጽ ሲያስመዘግብ አባልነቱ ይረጋገጥለታል።
በዚህም መሠረት፦
- በኒኦ ሶሳይቲ ዓላማዎችና ግቦች የሚያምን፤
-እድሜው ከ18 ዓመት እና ከዚያም በላይ የሆነ፣
- የኒኦ ሶሳይቲ የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በጠቅላላ ጉባዔውና በሥራ አመራር ምክር ቤቱ አማካይነት በየጊዜው የሚወጡ ህጎችን፤ መመርያና ደንቦችን እንዲሁም ሌሎችንም የሶሳይቲውን ሕግጋቶች ሁሉ የሚቀበልና ተግባራዊ የሚያደርግ፣
- በጠቅላላ ጉባዔውና በሥራ አመራር ምክር ቤቱ አባላት በየጊዜው ስምምነት የሚደረግባቸውን ክፍያዎችና መዋጮዎች የሚከፍል፤
-በህግ መብቱ/ቷ ያልተገፈፈ፤
- አባልነትን በውርስ፤ በስጦታ እና በወኪል ለሌላ ሰው ማስተላለፍ እንደማይቻል አውቆ የተረዳ፤
-የኒኦ ሶሳይቲ አባል ወይም ሠራተኛ በመሆኑ ብቻ በድርጅቱ ንብረት ላይ ከአባልነት መብት ያለፈ መብት የሌለው መሆኑን የተስማማ፤
- እውቀቱን፤ ልምዱን፤ ጉልበቱን፤ ጊዜውን፤ ገንዘቡን፤ ለኒኦ ሶሳይቲ በፈቃዱ ለማበርከት የተስማማ፤
-ከዘረኝነት፤ከጎሰኝነት፤ ከፖለቲካ አመለካከት፤ ከሐይማኖት፤ ከቋንቋ እና ከማንኛውም አድል ኦያዊ ሁኔታዎች የጸዳ፤
-የማንንም ሰው መብቶችንና ጥቅሞችን የማይጻረር፤
-ከኒኦ ሶሳይቲ አስተዳደራዊ ወጪዎች ውጪ በበጎ ፈቃድ ላበረከተ አገልግሎት ልዩ ጥቅም ወይም ክፍያ የማይጠይቅ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አባል መሆን ይችላል።
የአባልነት አምስቱ ደረጃዎች
1. መስራች አባላት
2. አባላት /መደበኛ አባላት/
3. ተጠባባቂ አባላት
4. እጩ አባላት
5. የክብር አባላት ናቸው።
sonn
ማንኛውም አባል መብቶቹንና ግዴታዎቹን አውቆ ይሠራል።
በዚህም የማህበሩ ዓላማዎች ወደ ተግባር እንዲተረጎሙ የተቻለውን ያህል በጎ ሚና ይጫወታል።