ለምን ደኃ ሆነን ?
ረጅሙን ታሪክ በአጭሩ ለመናገር ያህል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ድህነት መንስኤዎች ስንፍና፤ ድንቁርና፤ ልመና፤ሙስና ፤ ምስፍና እና አፈና ናቸው ። እነዚህ ስድስት የድህነት መንስኤዎች አሥር የድህነት መገለጫዎችን ያንጸባርቃሉ። የሥራና የትምህርት እጦትን፤ የጦርነትና የግጭት ችግሮችን፤ የአየር ንብረት መዛባትን፤ ማህበራዊ ኢ-ፍትሓዊነትን፤ የምግብና የውኃ እጥረትን፤ የመሠረተ-ልማትና የመንግስት ድጋፍ ጉድለትን፤ የጤና እንክብክቤ አለመኖርን፤ የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን ያስከትላሉ። ለእነዚህ እጥረቶችና እጦቶች መጋለጥ አስከፊ ድህነት ውስጥ መውደቅን ያረጋግጣል።
ስለዚህ ያደጉ አገሮች ከስንፍና ይልቅ ትጋትን፤ ከድንቁርና ይልቅ ዕውቀትን ፤ ከልመና ይልቅ ሰርቶ ማግኘትን፤ ከሙስና ይልቅ ታማኝነትን፤ ከምስፍና ይልቅ ዴሞክረሲን፤ ከአፈና ይልቅ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ለማደግ ችለዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብም ይህንን ለማድረግ መወሰን አለበት። እንደ ሕዝብ በመሰባሰብና በመደራጀት የራሱን ዊዝደም በመጠቀም፤ በተፈጥሮ ጸጋው በመገልገል፤ ከድህነት መውጣት አለበት። ሌላ ሰው መጥቶ ከድህነት ጎትቶ እንዲያወጣው መጠበቅ የለበትም። እራሱን በራሱ ከችጋር ማላቀቅ አለበት። የኒኦ ሶሳይቲ መነሻ ሃሳብ ይኼው ነው። በራሳችን ለራሳችን ከድህነት አዘቅት መውጣት!!ምክንያቱም የሁሉም ችግሮቻችን ምንጭ ድህነት ስለሆነ።
A D V A N C I N G
E T H I O P I A
ራእይ
እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ2040
ዓ.ም ለ1/4ኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንጀራ ምንጭ መሆን::
ተ ል ዕ ኮ
ከ21ኛ ክፍለ ዘመን ጋራ የሚራመዱ ሰዎችን በማሰባሰብና በማህበረሰብ ማዕቀፍ በማደራጀት፤ በተለያዩ የሙያ፤የሥራና የጥናት ዘርፎች ላይ በተግባር እንዲሰማሩ በማብቃት የድርሻቸውን አገራዊ አስተዋጽኦ ወደላቀ ደረጃ እንዲያደርሱ የማስቻል፤
መጥፎም ሆነ ጥሩ ፤ ክፉም ሆነ ደግ፤ ጠቃሚም ሆነ ጎጂ ያለው ታሪካችን የጋራችን ነው። የማንነታችን መግለጫ፤ የእኛነታችን ማስረጃ ነው።
መጥፎም ሆነ ጥሩ ፤ ክፉም ሆነ ደግ፤ ጠቃሚም ሆነ ጎጂ ያለው ታሪካችን የጋራችን ነው። የማንነታችን መግለጫ፤ የእኛነታችን ማስረጃ ነው።
መመጽወትን የመሰለ ቅስም ሰባሪ የለም። እኛ ድሆች ነን እያልን ለድህነታችን ሰበብ እየሳብን፤ ለድህነታችን ዕውቅና እየሰጠን ብዙ ዓመታቶችን አሳልፈናል። አሳፋሪ ነው። ሌሎች እየመገቡን ከድህነት እንዲያወጡን የምንጠብቅ ከሆነ ሰነፎች ነን። ስንፍና ፈጣሪም አይወድም። ስለዚህ ድህነትን መጥላት ብቻ ሳይሆን ድህነትን መክላት ግዴታችን መሆን አለበት።
የድህነት መድኃኒት ሥራ ነው።ኑ በጋራ እንሥራ!!
s o o n...
Telephone: +1510 345 9997
E-mail: admin@myneosociety.org
Address: 3838Turquoise Way, Oakland, CA, 94609